መሳፍንት 19:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ ካራ አነሣ፤ ዕቅብቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለዐሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ ሰደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቱ እንደ ደረሰም ቢላዋ አንሥቶ ቁባቱን ዐሥራ ሁለት ቦታ በመቈራረጥ ወደ እስራኤል ምድር ሁሉ ሰደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱ እንደደረሰም ቢላዋ አንሥቶ ቁባቱን ዐሥራ ሁለት ቦታ በመቈራረጥ ወደ እስራኤል ምድር ሁሉ ሰደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም በደረሰ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ ቢላዋም አንሥቶ የቊባቱን ሬሳ ዐሥራ ሁለት ቦታ ቈራረጠው፤ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዳንድ ቊራጭ ላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቤቱም በመጣ ጊዜ ካራ አነሣ፥ ቁባቱንም ይዞ ከአጥንቶችዋ መለያያ ላይ ለአሥራ ሁለት ቈራርጦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ ሰደደ። |
ጥምዱንም በሬዎች ወስዶ በየብልታቸው ቈራረጣቸው፤ ወደ እስራኤልም ዳርቻ ሁሉ በመልእክተኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ፥ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግበታል” አለ። ድንጋጤም በሕዝቡ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ።