ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
መሳፍንት 19:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፣ ጥቂት የከተማዪቱ ምናምንቴ ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፣ “ዝሙት እንድንፈጽምበት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብዣው ላይ እየተደሰቱ ሳለ፥ ጥቂት የከተማይቱ ወስላቶች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም እየደበደቡ፥ “ዝሙት እንድንፈጽም በት ቤትህ የገባውን ሰው አውጣው” በማለት የቤቱ ባለቤት በሆነው ሽማግሌ ላይ ጮኹበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እየተደሰቱ ሳለም ከከተማይቱ የመጡ ጋጠወጦች በድንገት ቤቱን ከበው በሩን መደብደብ ጀመሩ፤ ሽማግሌውንም “ያንን ወደ ቤትህ የገባውን ሰው ግብረ ሰዶም እንድንፈጽምበት አውጣልን!” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ ወስላቶች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ በሩንም ይደበድቡ ነበር፥ ባለቤቱንም ሽማግሌውን፦ ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን አሉት። |
ዳግመኛም ወልደ አዴር እንዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝቤና ሠራዊቴ ሁሉ ሀገርህን ሰማርያን ባያጠፉት፥ የቀበሮም ማደሪያ ባያደርጉት አማልክት እንዲህ ያድርጉብኝ፤ እንዲህም ይግደሉኝ።”
ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፤ ታናሽቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።
እስራኤል ከጊብዓ ዘመን ጀምሮ ኀጢአትን ሠርቶአል፤ በዚያም ጸንተዋል፤ በጊብዓ ላይ ጦር አይደርስባቸውምን? መጥቶም የዐመፅ ልጆችን ገሠጻቸው፤
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ክርስቶስን ከቤልሆር ጋር አንድ የሚያደርገው ማን ነው? ወይስ ምእመናንን ከመናፍቃን ጋር አንድ ወገን የሚያደርጋቸው ማን ነው?
ክፋተኞች ሰዎች ከእናንተ ዘንድ ወጥተው፦ ሄደን የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ ሲሉ ወሬ ብትሰማ፥
እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
ከዚህም በኋላ ልባቸውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ከእስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶምሶንንም ከእስር ቤት ጠሩት፤ በፊታቸውም ተጫወተ፤ ተዘባበቱበትም፤ በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት።
የገባዖንም ሰዎች ተነሡብን፤ ቤቱንም በሌሊት በእኛ ላይ ከበቡት፤ ሊገድሉኝም ወደዱ፤ ዕቅብቴንም አዋረድዋት፤ አመነዘሩባትም፤ እርስዋም ሞተች።
እኔም ዕቅብቴን ይዤ በመለያያዋ ቈራረጥኋት፤ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ስንፍና ስለ ሠሩ ወደ እስራኤል ርስት አውራጃ ሁሉ ሰደድሁ።
በዚህ ክፉ ሰው በናባል ላይ ጌታዬ ልቡን እንዳይጥል እለምናለሁ፤ እንደ ስሙ እንዲሁ እርሱ ነው፤ ስሙ ናባል ነው፤ ስንፍናም አድሮበታል፤ እኔ ባሪያህ ግን አንተ የላክሃቸውን ብላቴኖችህን አላየሁም።