La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሽማ​ግ​ሌ​ውም ሰው፥ “ሰላም ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ የም​ት​ሻ​ው​ንም ሁሉ እኔ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ በአ​ደ​ባ​ባይ ግን አት​ደር” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሽማግሌውም፣ “ኑ ግቡ በቤቴም ዕደሩ፤ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አቀርባለሁ፤ በአደባባይ ግን አትደሩ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሽማግሌውም፥ “ኑ ግቡ በቤቴም እደሩ፤ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አቀርባለሁ፤ በዐደ ባባይ ግን አትደሩ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሽማግሌውም “ሰላም ለአንተ ይሁን! እነሆ ወደ ቤቴ ግባ! እኔ ማደሪያ አዘጋጅልሃለሁ፤ በዚህ አደባባይ ላይ ማደር አይገባህም” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሽማግሌውም፦ ሰላም ከአንተ ጋር ይሁን፥ የምትሻውንም ሁሉ እኔ እሰጥሃለሁ፥ በአደባባይ ግን አትደር አለው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 19:20
15 Referencias Cruzadas  

መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


“ሰላ​ምን እተ​ው​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሰላ​ሜ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ሰ​ጣ​ችሁ ዓለም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጠው አይ​ደ​ለም፤ ልባ​ችሁ አይ​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ፍ​ሩም።


በች​ግ​ራ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንን ለመ​ር​ዳት ተባ​በሩ፤ እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አዘ​ው​ትሩ።


ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።


ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።


እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አት​ርሱ፤ በዚህ ምክ​ን​ያት ሳያ​ውቁ መላ​እ​ክ​ትን በእ​ን​ግ​ድ​ነት ለመ​ቀ​በል ያታ​ደሉ አሉና።


ያለ ማንጐራጐር እርስ በርሳችሁ እንግድነትን ተቀባበሉ፤


ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ አት​ፍራ፤ አት​ሞ​ትም” አለው።


እን​ዲ​ህም በሉት፥ “ደኅ​ን​ነ​ትና ሰላም ለአ​ን​ተና ለቤ​ትህ፥ ለአ​ን​ተም ለሆ​ኑት ሁሉ ይሁን።