መሳፍንት 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው ብላቴና እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ ከሚያስፈልገን ሁሉ አንዳችም አላጣንም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ እኛ ባሮችህ ለእኔም ሆነ ለገረድህ፣ ዐብሮን ላለውም ወጣት እንጀራና የወይን ጠጅ ይዘናል፤ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ እኛ ባሮችህ ለእኔም ሆነ ለገረድህ፥ አብሮን ላለውም ወጣት እንጀራና የወይን ጠጅ ይዘናል፤ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ግን ለአህዮቻችን ገፈራና ገለባ፥ ለቊባቴና ለእኔ እንዲሁም ለአገልጋዬ እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ የሚያስፈልገንን ሁሉ ይዘናል፤ ምንም ያጣነው ነገር የለም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፥ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው አሽከር እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፥ አንዳችም አላጣንም አለው። |
እርሱም ተቀብሎ አሳደራቸው፤ በማግሥቱም ተነሥቶ አብሮአቸው ሄደ፤ በኢዮጴ ከተማ ከሚኖሩት ወንድሞችም አብረውት የሄዱ ነበሩ።
እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን።
በኢያቡስም አንጻር ገና ሳሉ ፀሐይዋ ተቈለቈለች፤ ብላቴናውም ጌታውን፥ “ና፤ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ እናቅና፤ በእርስዋም እንደር” አለው።
እርሱም፥ “እኛ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ማዶ እናልፋለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔምም ሄጄ ነበር፥ አሁንም ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፤ በቤቱም የሚያሳድረኝ አጣሁ፤