ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ።
መሳፍንት 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እኛ ከይሁዳ ቤተ ልሔም ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም ሀገር ማዶ እናልፋለን፤ እኔ ከዚያ ነኝ፤ ወደ ይሁዳ ቤተ ልሔምም ሄጄ ነበር፥ አሁንም ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፤ በቤቱም የሚያሳድረኝ አጣሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኛ የመጣነው ከይሁዳ ከቤተ ልሔም ርቆ ከሚገኘው ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር ነው፤ ከይሁዳ ከቤተ ልሔም ነበርሁ፤ አሁን ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄዳለሁ፤ ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ሰው አላገኘሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየውም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኛ የመጣነው ከይሁዳ ቤተልሔም ርቆ ከሚገኘው ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር ነው፤ ከይሁዳ ቤተልሔም ነበርሁ፤ አሁን ወደ ጌታ ቤት እሄዳለሁ፤ ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ሰው አላገኘሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋዊውም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ነበርን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤትና በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ቤታችን ለመድረስ በጒዞ ላይ ነን፤ ወደ ቤቱ ወስዶ የሚያሳድረን እስከ አሁን አላገኘንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እኛ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ወደ ተራራማው ወደ ኤፍሬም አገር ማዶ እናልፋለን፥ እኔ ከዚያ ነኝ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ይሁዳ ሄጄ ነበር፥ አሁንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እሄዳለሁ፥ በቤቱም የሚያሳድረኝ አጣሁ፥ |
ፊትህን ከእኔ አትመልስ፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ አምላኪዬና መድኀኒቴ ሆይ፥ ቸል አትበለኝ።
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ፤ በዚያም የምስክሩን ድንኳን ተከሉ፤ ምድሩም ጸጥ ብሎ ተገዛላቸው።
ዐይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፤ ሽማግሌውም፥ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?” አለው።
ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው ብላቴና እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ ከሚያስፈልገን ሁሉ አንዳችም አላጣንም” አለው።
በአራተኛውም ቀን ማልደው ተነሡ፤ እርሱም ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱም አባት አማቹን፥ “ሰውነትህን በቁራሽ እንጀራ አበርታ፤ ከዚያም በኋላ ትሄዳላችሁ” አለው።
የእስራኤልም ልጆች ተነሥተው ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርንም፥ “የብንያምን ልጆች ለመውጋት መሪ ሆኖ ማን ይውጣልን?” ብለው ጠየቁት፤ እግዚአብሔርም፥ “ይሁዳ መሪ ይሁን” አለ፤
ያም ሰው በሴሎ ይሰግድ ዘንድ፥ ለሠራዊት ጌታም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ከከተማው ከአርማቴም በየዓመቱ ይወጣ ነበር። የእግዚአብሔርም ካህናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ።
በየዓመቱም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚወጣበት ጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ እርስዋም ትበሳጭና ታለቅስ ነበር። እህልም አትበላም ነበር።