መሳፍንት 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢያቡስም አንጻር ገና ሳሉ ፀሐይዋ ተቈለቈለች፤ ብላቴናውም ጌታውን፥ “ና፤ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ እናቅና፤ በእርስዋም እንደር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኢያቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፣ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ የቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፥ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ የቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ኢያቡስ በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፤ አሽከሩም ጌታውን “ና እባክህ ወደ እዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንመለስና እዚያ እንደር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢያቡስም በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፥ አሽከሩም ጌታውን፦ ና፥ ወደዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ፥ እናቅና፥ በእርስዋም እንደር አለው። |
ዳዊትና ሰዎቹም በሀገሩ ውስጥ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሴዎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም ዳዊትን፥ “ወደዚህ አትገባም” አሉት። ዕውሮችና አንካሶችም ወደዚህ አትገባም ብለው ተቃወሙት።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሴዎናውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።
ሰውዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፤ ተነሥቶም ሄደ፤ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፤ ዕቅብቱም ከእርሱ ጋር ነበረች።
ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ ለእኔና ለገረድህ ከባሪያዎችህም ጋር ላለው ብላቴና እንጀራና የወይን ጠጅ አለን፤ ከሚያስፈልገን ሁሉ አንዳችም አላጣንም” አለው።