ዳዊትና ሰዎቹም በሀገሩ ውስጥ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሴዎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም ዳዊትን፥ “ወደዚህ አትገባም” አሉት። ዕውሮችና አንካሶችም ወደዚህ አትገባም ብለው ተቃወሙት።
መሳፍንት 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውዬው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፤ ተነሥቶም ሄደ፤ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለችው ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፤ ዕቅብቱም ከእርሱ ጋር ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ ኢያቡስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋዊው ግን ያንን ሌሊት እዚያ ለማሳለፍ አልፈለገም፤ ስለዚህ እርሱ፥ ቊባቱና አገልጋዩ ተነሥተው ጒዞ ጀመሩ፤ ኮርቻ የተጫኑ ሁለት አህዮችም ነበሩአቸው፤ ቀኑም በመሸ ጊዜ የቡስ ተብላ ትጠራ ወደነበረችው ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ አጠገብ ደረሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮው ግን በዚያ ሌሊት ለማደር አልፈቀደም፥ ተነሥቶም ሄደ፥ ኢየሩሳሌምም ወደ ተባለች ወደ ኢያቡስ ፊት ለፊት ደረሰ። ከእርሱም ጋር ሁለት የተጫኑ አህዮች ነበሩ፥ ቁባቱም ከእርሱ ጋር ነበረች። |
ዳዊትና ሰዎቹም በሀገሩ ውስጥ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሴዎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም ዳዊትን፥ “ወደዚህ አትገባም” አሉት። ዕውሮችና አንካሶችም ወደዚህ አትገባም ብለው ተቃወሙት።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወጣል፤ ድንበሩም በሰሜን በኩል በራፋይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባሕር በኩል ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ይወጣል፤
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ሰውዬውም ከዕቅብቱና ከብላቴናው ጋር ለመሄድ ተነሣ፤ የብላቴናዪቱ አባት አማቱም፥ “እነሆ፥ መሽትዋል፤ ፀሐዩም ሊጠልቅ ደርሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚህም ተቀመጥ፤ ልብህም ደስ ይበለው፤ በጥዋትም መንገዳችሁን ትገሠግሣላችሁ፤ ወደ ቤትህም ትገባለህ” አለው።