ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እንዳለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በልባቸው መራሮችና ኀያላን መሆናቸውን አባትህንና ሰዎቹን ታውቃለህ፤ አባትህ አርበኛ ነው፤ ሕዝቡንም አያሰናብትም።
መሳፍንት 18:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳንም ልጆች እንዲህ አሉት፥ “የተቈጡ ሰዎች እንዳያገኙህና ነፍስህም፥ የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህ በእኛ መካከል አይሰማ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳን ሰዎች፣ “አትሟገተን፤ አለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጕዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተ ሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳን ሰዎች፥ “አትሟገተን፤ ያለዚያ የተቈጡ ሰዎች ጉዳት ላይ ይጥሉሃል፤ አንተም ቤተሰብህም ሕይወታችሁን ታጣላችሁ” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዳን የመጡትም ሰዎች “የተቈጡ ሰዎች አደጋ እንዳይጥሉብህና የአንተንና የቤተሰብህን ሕይወት እንዳታጣ በመካከላችን ምንም ድምፅ ባታሰማ ይሻልሃል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳንም ልጆች፦ የተቈጡ ሰዎች እንዳይወድቁብህ ነፍስህም የቤተ ሰቦችህም ነፍስ እንዳይጠፋብህ፥ ድምፅህን በእኛ መካከል አታሰማ አሉት። |
ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እንዳለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በልባቸው መራሮችና ኀያላን መሆናቸውን አባትህንና ሰዎቹን ታውቃለህ፤ አባትህ አርበኛ ነው፤ ሕዝቡንም አያሰናብትም።
እርሱም፥ “የሠራኋቸውን አማልክቴን፥ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፤ ለእኔ ምን ተዋችሁልኝ? እናንተስ፦ ለምን ትጮኻለህ እንዴት ትሉኛላችሁ?” አለ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።