እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
መሳፍንት 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፤ የዳንም ልጆች ፊታቸውን መልሰው ሚካን፥ “የምትጮኸው ምን ሆነህ ነው?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከበስተኋላቸው ሆነው ሲጮኹባቸውም፣ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፣ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆንህና ነው?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከበሰተኋላቸው ሆነው ሲጮሁባቸውም፥ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፥ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆነህ ነው?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደነፋባቸው፤ ከዳን የመጡትም ሰዎች ወደ ኋላ መለስ ብለው ሚካን “ምን ሆነሃል? ይህን ሁሉ ሰውስ የሰበሰብከው ለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዳንም ልጆች ጮኹ፥ የዳንም ልጆች ፊታቸውን መልሰው ሚካን፦ የምትጮኸው ምን ሆነህ ነው? አሉት። |
እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
ንጉሡም፥ “ምን ሆነሻል?” አላት፤ እርስዋም፥ “ይህች ሴት፦ ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ፤ ነገም ልጄን እንበላለን አለችኝ።
እርሱም፥ “የሠራኋቸውን አማልክቴን፥ ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፤ ለእኔ ምን ተዋችሁልኝ? እናንተስ፦ ለምን ትጮኻለህ እንዴት ትሉኛላችሁ?” አለ።
እነሆም፥ ሳኦል ከእርሻው አርፍዶ መጣ፤ ሳኦልም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።