መሳፍንት 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ተመልሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገንዘቡንና ሀብቱንም ሁሉ፥ በፊታቸው አድርገው ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ሕፃናታቸውን፣ የከብቶቻቸውን መንጋና ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ፊት በማስቀደም ተመልሰው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሕፃናታቸውን፥ የከብቶቻቸውን መንጋና ሀብታቸውን ሁሉ ወደ ፊት በማስቀደም ተመልሰው ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ልጆቻቸውን ከብቶቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ከፊት አስቀድመው ወደ ኋላ በመመለስ ጒዞአቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ዞረው ሄዱ፥ ሕፃናቶችንና ከብቶችን ዕቃዎችንም በፊታቸው አደረጉ። |
ካህኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉዱንም፥ ተራፊሙንም፥ የተቀረፀውንም ምስል፥ ቀልጦ የተሠራውንም ምስል ወሰደ፤ በሕዝቡም መካከል ገባ።