La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም፥ “ዝም በል፤ እጅ​ህ​ንም በአ​ፍህ ላይ ጫን፤ ከእ​ኛም ጋር ና፥ አባ​ትና ካህ​ንም ሁን​ልን፤ ለአ​ንድ ሰው ቤት ካህን መሆን ወይስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ለነ​ገ​ድና ለወ​ገን ካህን መሆን ማና​ቸው ይሻ​ል​ሃል?” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “ዝም በል! አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋራ ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተ ሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም፥ “ዝም በል አንዲት ቃል እንዳትተነፍስ፤ ከእኛ ጋር ሁን፤ አባትም ካህንም ሁነን፤ ለአንተስ የአንድ ቤተሰብ ካህን ከመሆን ይልቅ በእስራኤል የአንዱ ነገድና ጐሣ ካህን ሆነህ ማገልገሉ አይሻልህምን?” አሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም “ዝም በል! አፍህን ዝጋ፤ ይልቅስ መጥተህ ካህናችንና አማካሪያችን ሁን፤ የአንድ ሰው ቤተሰብ ካህን ከምትሆን የአንድ እስራኤላዊ ነገድ ካህን መሆን አይሻልህምን?” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ ዝም በል፥ እጅህንም በአፍህ ላይ ጫን፥ ከእኛም ጋር መጥተህ አባትና ካህን ሁንልን፥ ለአንድ ሰው ቤት መሆን ወይስ በእስራኤል ዘንድ ለነገድና ለወገን ካህን መሆን ማናቸው ይሻልሃል? አሉት።

Ver Capítulo



መሳፍንት 18:19
12 Referencias Cruzadas  

ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባያ​ቸው ጊዜ ኤል​ሳ​ዕን፥ “አባቴ ሆይ፥ ልግ​ደ​ላ​ቸ​ውን?” አለው።


ወደ እኔ ተመ​ል​ከቱ፥ ተደ​ነ​ቁም፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በጕ​ን​ጫ​ችሁ ላይ አኑሩ።


ኀያ​ላ​ኑም ከመ​ና​ገር ዝም አሉ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በአ​ፋ​ቸው ላይ ጫኑ።


አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥


አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም ‘አባት’ ብላችሁ አትጥሩ።


ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


እነ​ዚ​ህም ሰዎች ወደ ሚካ ቤት ገብ​ተው የተ​ቀ​ረ​ፀ​ውን ምስል፥ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን ምስ​ልም ወሰዱ፤ ካህ​ኑም፥ “ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


ካህ​ኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ምስል ወሰደ፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ገባ።