La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወጥ​ተ​ውም በይ​ሁዳ ቂር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰፈሩ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፤ እነ​ሆም፥ ቦታዉ ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም በስ​ተ​ኋላ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓይሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚሁ የተነሣ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወጥተውም በይሁዳ ምድር ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፤ እንግዲህ ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ያለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር መባሉ ከዚህ የተነሣ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ወጥተው በይሁዳ በምትገኘው ከቂርያትይዓሪም በስተ ምዕራብ ሰፈሩ፤ ያ ስፍራ እስከ አሁን የዳን ሰፈር ተብሎ የሚጠራውም ስለዚህ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወጥተውም በይሁዳ ባለችው በቂርያትይዓሪም ሰፈሩ፥ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የዳን ሰፈር ተብሎ ተጠራ፥ እነሆም፥ ከቂርያትይዓሪም በስተ ኋላ ነው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 18:12
10 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም አወ​ጣት። ለእ​ርሷ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ድን​ኳን አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላት ነበ​ርና።


ቴቆ፥ ኤፍ​ራታ፥ ይኽ​ች​ውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎ​ርም፥ ኤጣ​ንም፥ ቁሎን፥ ጠጦ​ንም፥ ሶብ​ሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነ​ኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ቅር​ያ​ት​በ​ኣል፥ ይኽ​ች​ውም የኢ​ያ​ርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ድን​በ​ሩም ከተ​ራ​ራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄ​ዳል፤ ወደ ዔፍ​ሮ​ንም ተራራ ይደ​ር​ሳል፤ ወደ ኢያ​ሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደ​ር​ሳል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሶ​ራ​ሕና በእ​ስ​ታ​ሔል መካ​ከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ይሄድ ጀመረ።


ከዳን ወገ​ንም የጦር ዕቃ የታ​ጠቁ ስድ​ስት መቶ ሰዎች ከዚያ ከሶ​ራ​ሕና ከእ​ስ​ታ​ሔል ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።


ከዚ​ያም ወደ ተራ​ራ​ማው ወደ ኤፍ​ሬም አገር አለፉ እስከ ሚካም ቤት ደረሱ።


በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪ​ምም ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልከው፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት መል​ሰ​ዋል፤ ወር​ዳ​ች​ሁም ወደ እና​ንተ ውሰ​ዱ​አት” አሉ።


የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት።