La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 16:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ህም በኋላ ልባ​ቸ​ውን ደስ ባለው ጊዜ፥ “በፊ​ታ​ችን እን​ዲ​ጫ​ወት ሶም​ሶ​ንን ከእ​ስር ቤት ጥሩት” አሉ። ሶም​ሶ​ን​ንም ከእ​ስር ቤት ጠሩት፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ተጫ​ወተ፤ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በ​ትም፤ በም​ሰ​ሶና በም​ሰ​ሶም መካ​ከል አቆ​ሙት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሰሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፥ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሶሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ እንዲጫወትልን ሶምሶንን ጥሩት አሉ ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፤ በፊታቸውም ተጫወተ፤ በምሰሶና በምሰሶ መካከል አቆሙት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልባቸውንም ደስ ባለው ጊዜ፦ በፊታችን እንዲጫወት ሶምሶንን ጥሩት አሉ። ሶምሶንንም ከግዞት ቤት ጠሩት፥ በፊታቸውም ተጫወተ፥ ተዘባበቱበትም፥ በምሰሶና በምሰሶም መካከል አቆሙት።

Ver Capítulo



መሳፍንት 16:25
23 Referencias Cruzadas  

አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


የጾም አዋ​ጅም ነገሩ፤ ናቡ​ቴ​ንም በሕ​ዝቡ ፊት በከ​ፍ​ተኛ ቦታ አስ​ቀ​መ​ጡት።


እነ​ሆም፥ በዓ​ልን፥ ደስ​ታ​ንና ሐሴ​ትን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም አረ​ዳ​ችሁ፤ “ነገ እን​ሞ​ታ​ለን፤ እን​ብላ፤ እን​ጠ​ጣም፤” እያ​ላ​ችሁ ሥጋን በላ​ችሁ፤ ወይ​ን​ንም ጠጣ​ችሁ።


ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤


የገ​ረ​ፉ​አ​ቸው፥ የዘ​በ​ቱ​ባ​ቸ​ውና ያሠ​ሩ​አ​ቸው ወደ ወህኒ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ውም አሉ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድ​ራ​ች​ንን ያጠ​ፋ​ውን፥ ከእ​ኛም ብዙ ሰው የገ​ደ​ለ​ውን ጠላ​ታ​ች​ንን አም​ላ​ካ​ችን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን እያሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን አመ​ሰ​ገኑ።


ሶም​ሶ​ንም የሚ​መ​ራ​ውን ብላ​ቴና፥ “ቤቱን የደ​ገ​ፉ​ትን ምሰ​ሶ​ዎች እደ​ገ​ፍ​ባ​ቸው ዘንድ እባ​ክህ አስ​ይ​ዘኝ” አለው፥ ብላ​ቴ​ና​ውም እን​ዳ​ለው አደ​ረ​ገ​ለት።


ካህ​ኑም በልቡ ደስ አለው፤ ኤፉ​ዱ​ንም፥ ተራ​ፊ​ሙ​ንም፥ የተ​ቀ​ረ​ፀ​ው​ንም ምስል፥ ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ምስል ወሰደ፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ገባ።


ሁለ​ቱም በአ​ንድ ላይ ተቀ​መጡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ሰው​ዬ​ውን፥ “ዛሬ ደግሞ ከዚህ እደር ልብ​ህ​ንም ደስ ይበ​ለው” አለው።


ሰው​ዬ​ውም ከዕ​ቅ​ብ​ቱና ከብ​ላ​ቴ​ናው ጋር ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት አማ​ቱም፥ “እነሆ፥ መሽ​ት​ዋል፤ ፀሐ​ዩም ሊጠ​ልቅ ደር​ሷል፤ ዛሬም እዚህ እደር፤ በዚ​ህም ተቀ​መጥ፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ለው፤ በጥ​ዋ​ትም መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ላ​ችሁ፤ ወደ ቤት​ህም ትገ​ባ​ለህ” አለው።


ወደ እር​ሻ​ውም ወጡ፤ ወይ​ና​ቸ​ው​ንም ለቀሙ፤ ጠመ​ቁ​ትም፤ የደ​ስ​ታም በዓል አደ​ረጉ፤ ወደ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ረገ​ሙት።