ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም፤ አልጸየፋቸውምም።
መሳፍንት 16:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የራሱም ጠጕር ከላጩት በኋላ ያድግ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ከተላጨ በኋላ ጠጕሩ እንደ ገና ማደግ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከተላጨ በኋላ ጠጉሩ እንደገና ማደግ ጀመረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቈረጠውም የራሱ ጠጒር እንደገና ማደግ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የራሱም ጠጉር ከላጩት በኋላ ያድግ ጀመር። |
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም፤ አልጸየፋቸውምም።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ስለ አገልጋዮቹም ይራራል፤ በያሉበት መሳለቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥ ኀይላቸውም እንደ ደከመ፥ በጠላትም እጅ እንደ ወደቁ አይቶአልና።
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።
የፍልስጥኤም መሳፍንትም፥ “አምላካችን ጠላታችንን ሶምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” እያሉ ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ይሠዉ ዘንድ፥ ደስም ይላቸው ዘንድ ተሰበሰቡ።