አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
መሳፍንት 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የዚያችን የአህያ መንጋጋ አጥንት ስንጥቃት ከፈተ፤ ከእርስዋም ውኃ ወጣ፤ እርሱም ጠጣ፤ ነፍሱም ተመለሰች፤ ከውኃ ጥሙም ዐረፈ። ስለዚህም የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ነቅዐ አጽመ መንሰክ” ተብሎ ተጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውሃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም በሌሒ ዐለት ሰነጠቀለት፤ ከዚያም ውኃ ወጣ፤ ሳምሶንም ያን ሲጠጣ በረታ፤ መንፈሱም ታደሰ። ስለዚህ ያ ምንጭ ዓይንሀቆሬሸ ተባለ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው በሌሒ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሌሂ ያለው ጐድጓዳ ቦታ ከፈተለት፤ ከእርሱም ውሃ ወጣ፤ በጠጣም ጊዜ መንፈሱ ተመልሶለት ተጠናከረ፤ ስለዚህም ያ ቦታ “ዐይን ሃቆሬ” የተባለ። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሂ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በሌሒ ያለውን አዘቅት ሰነጠቀ፥ ከእርሱም ውኃ ወጣ፥ እርሱም ጠጣ፥ ነፍሱም ተመለሰች፥ ተጠናከረም። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ዓይንሀቆሬ ብሎ ጠራው፥ ይህም እስከ ዛሬ ድረስ በሌሒ አለ። |
አጋርም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራራህልኝ አንተ ነህ፤ የተገለጠልኝን በፊቴ አይችዋለሁና።”
እነርሱም ዮሴፍ ያላቸውን፥ የተናገራቸውንም ነገር ሁሉ ነገሩት፤ ይወስዱት ዘንድ ዮሴፍ የላካቸውን ሰረገሎች በአየ ጊዜ የአባታቸው የያዕቆብ ልቡ፥ መንፈሱም ታደሰ።
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
በደረቅ መሬት ላይ ለሚሄድና ለተጠማ ውኃን እሰጣለሁ፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፥ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አኖራለሁ፤
ከበለሱም ጥፍጥፍ ቍራጭ ሰጡትና በላ፤ ነፍሱም ወደ እርሱ ተመለሰች፤ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም ነበርና።