La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባ​ቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፤ ጐበ​ዞ​ችም እን​ዲሁ ያደ​ርጉ ነበ​ርና ሶም​ሶን በዚያ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረገ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በነበረው የሙሽራ ወግ መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በወጣቶች የተለመደ በነበረው መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አባቱ ወደ ሴቲቱ ቤት በሄደ ጊዜ፥ ሶምሶን በዚያ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ ይህም ዐይነቱ ግብዣ በወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነበር፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባቱም ወደ ሴቲቱ ወረደ፥ ጎበዞችም እንዲህ ያደርጉ ነበርና ሶምሶን በዚያ በዓል አደረገ።

Ver Capítulo



መሳፍንት 14:10
8 Referencias Cruzadas  

ላባም የዚ​ያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፥ ሰር​ግም አደ​ረገ።


ሰነ​ፎች ሰዎች እን​ጀ​ራን ለሣቅ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ የወ​ይን ጠጅም ሕያ​ዋ​ንን ደስ ያሰ​ኛል፥ ሁሉም ለገ​ን​ዘብ ይገ​ዛል።


አሳ​ዳ​ሪ​ውም ያን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ውኃ ቀምሶ አደ​ነቀ፤ ከወ​ዴት እንደ መጣም አላ​ወ​ቀም፤ የቀ​ዱት አሳ​ላ​ፊ​ዎች ግን የወ​ይን ጠጅ የሆ​ነ​ውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃ​ዉን የሞሉ እነ​ርሱ ነበ​ሩና።


መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።


ከዚ​ህም በኋላ ፈር​ተው ሠላሳ ሰዎ​ችን በእ​ርሱ ላይ ሾሙ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ተቀ​መጡ።


ወስ​ዶም በላ፤ እየ​በ​ላም ሄደ፤ ወደ አባ​ቱና ወደ እና​ቱም ደረሰ፤ ሰጣ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ማሩ​ንም ከአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ እን​ዳ​ወ​ጣው አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።