በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
መሳፍንት 13:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኑሄም ሚስቱን፥ “እግዚአብሔርን አይተናልና ሞትን እንሞታለን” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኑሄም ሚስቱን፣ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቱንም፥ “እግዚአብሔርን ስላየን ያለ ጥርጥር እንሞታለን” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኑሄ ሚስቱን “እግዚአብሔርን ስላየን በእርግጥ እንሞታለን!” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኑሄም ሚስቱን፦ እግዚአብሔርን አይተናልና ሞት እንሞታለን አላት። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም የቆመበትን ቦታ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ፥ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከግብፅ ከአንተ የጸኑትን ታላላቆቹን አሕዛብ በፊትህ እንዲያወጣ፥ አንተንም እንዲያገባህ፥ ምድራቸውንም ርስት አድርጎ እንዲሰጥህ፥
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴዎንም፥ “አቤቱ! አምላኬ ሆይ! ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ።