ኢዮብ 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውነቶቼ ሁሉ ተነዋወጡ፤ እንግዲህ ንጹሕ አድርገህ እንደማትተወኝ አውቃለሁ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣ መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁና ከመከራዬ ሁሉ የተነሣ እፈራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ንጹሕ አድርጎ እንደማይቈጥረኝ ስለማውቅ፥ መከራና ሥቃይ ይመጣብኛል ብዬ እፈራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁና ከመከራዬ ሁሉ እፈራለሁ። |
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።