አሁንም፥ ፊታችሁን አይቼ ሐሰት አልናገርም።
“አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤ ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?
አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፥ በፊታችሁም ሐሰት አልናገርም።
እባካችሁ ፊቴን ተመልከቱ፤ በፊታችሁ እዋሻለሁን?
ንግግር አታብዛ፤ የሚከራከርህ የለምና።
እናንተ ግን የዐመፅ ባለ መድኀኒቶች፥ ሁላችሁም የክፋት ፈዋሾች ናችሁ።
እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ ነህ የሚለኝ፥ ነገሬንስ እንደ ኢምንት የሚያደርገው ማን ነው?”
አንደበቴ ዐመፅን አይናገርም፤ ነፍሴም የዐመፅ አሳብን አትማርም፤
ልቤም ንጹሕ ነገርን ያስባል፥ የከንፈሮችም ማስተዋል ንጹሕ ነገርን ይመረምራል።
ቃሌ ሐሰት ያይደለ እውነት ነው። አንተም የዐመፅ ቃላትን አትሰማም።