“አስተምሩኝ፥ እኔም አዳምጣችኋለሁ፤ የተሳሳትሁትም ካለ አስረዱኝ።
“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።
አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፥ የተሳሳትሁትንም ንገሩኝ።
“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ስሕተቴንም አስረዱኝ።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ኀጢኣተኛ እንድሆን አታስተምረኝ፤ ለምንስ እንደዚህ ፈረድህብኝ?
ኀጢአቶችና በደሌ ምን ያህል ናቸው? ምን ያህል እንደ ሆኑ አስታውቀኝ።
እነሆ፥ ንግግሬን አድምጡኝ፤ የምትናገሩትን ነገር እስክትመረምሩ ድረስ እየሰማችሁት እነግራችኋለሁ።
“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥ ነገሬንም አድምጥ።
እኔ ራሴ አያለሁ፥ ኀጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰትንም ተናግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እንዳልሠራ አንተ አሳየኝ።
እነሆ፥ ይህን ዐውቀን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፤ አንተ ግን አንዳች ሠርተህ እንደ ሆነ ለራስህ ዕወቅ።”
ወይስ ከጠላቶች እጅ ታስጥሉኝ ዘንድ ከኀይለኞችም እጅ ታድኑኝ ዘንድ።
የእውነተኛ ሰው ቃል ሐሰትን ይመስላል፥ ከእናንተ ዘንድ ኀይልን የምጠይቅ አይደለምና።
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፈራዋለች፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደነግጣሉ።
ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።