“እነሆ፥ በአንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
“አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤
አንተን እንደሠራሁ የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
“እኔ አንተንና ጒማሬን ፈጥሬአለሁ፤ ጉማሬውም እንደ በሬ ሣር ይበላል።
ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
ተራራውን እንደ መሰምሪያው ይመለከተዋል፥ ለምለሙንም ሁሉ ይፈልጋል።
በዚያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ታድንህ ዘንድ እንድትችል፥ እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ።
እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፤ ኀይሉም በሆዱ እንብርት ውስጥ ነው።
ይህ የእግዚአብሔር የፍጥረቱ አውራ ነው። ከተፈጠረም በኋላ መላእክት ሣቁበት።
ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም በሜዳው ላሉ እንስሳት በጥልቁ ስፍራ ደስታን ያደርጋል።
ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልተወም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታቱን ገሠጸ።