ኢዮብ 39:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ጆፌ አሞራስ ልጆቹን አቅፎ ያድራልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ ጐጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣ በአንተ ትእዛዝ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንስር ከፍ ከፍ የሚለው፥ ቤቱንም በከፍታ ላይ የሚያደርገው በአንተ ተእዛዝ ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንስርን ወደ ላይ ወጥቶ በከፍተኛም ቦታ ላይ ጎጆውን የሚሠራው አንተ አዘኸው ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን? |
በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ እንደ ንስር ክንፍም እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
በብብታቸው እንደ መሬት፤ በእግዚአብሔርም ቤት እንደ ንስር ይመጣል። ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና።