ቀስትና ጦር በእርሱ ላይ ይበረታሉ፥
ከሚብረቀረቀው ጦርና ዐንካሴ ጋራ፣ የፍላጻው ኰረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል።
በእርሱ ላይ የፍላጻ ኮረጆ፥ የሚብለጨልጭ ጦርና ሰላጢን ያንኳኳሉ።
የሚጋልቡአቸው ጦረኞች የያዙአቸው የጦር መሣሪያዎች በፀሐይ እየተብለጨለጩ እርስ በርሳቸው ሲፋጩ ይሰማል።
በእርሱ ላይ የፍላጻ ኮረጆና ብልጭልጭ የሚል ጦር ሰላጢንም ያንኳኳሉ።
በሚገናኘው ፍላጻ ላይ ይስቃል። ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
በቍጣውም መሬትን ያጠፋል፤ የመለከትም ድምፅ እስከሚሰማው አያምንም።
የኃያላኑ ጋሻ ቀልቶአል፥ ጽኑዓንም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱም በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፣ የጦሩም ሶመያ ይወዛወዛል።