ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን፥ “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎች በላች።
ኢዮብ 38:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መብረቁን ትልከዋለህን? እርሱስ ይሄዳልን? ደስታህስ ምንድን ነው ይልሃልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም መብረቆችን መስደድ ትችላለህ? እነርሱስ፣ ‘እነሆ፤ እዚህ አለን’ ይሉሃል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መብረቆች ሄደው፦ ‘እነሆ፥ እዚህ አለን’ ይሉህ ዘንድ፥ ልትልካቸው ትችላለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መብረቅ በአንተ ትእዛዝ ይበርቃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብረቆች ሄደው፦ እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድ፥ ልትልካቸው ትችላለህን? |
ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን፥ “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎች በላች።
እነሆ፥ እሳት ከሰማይ ወርዳ የፊተኞቹን ሁለቱን የአምሳ አለቆችና አምሳ አምሳውን ሰዎቻቸውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን።”
ሙሴም፥ “ለፈርዖን ከከተማ በወጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱም ለእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐድጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረዶውም፥ ዝናቡም ደግሞ አይወርድም።
የጌታንም ድምፅ፥ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች።