La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 37:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ ቁም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ተገ​ሠጽ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ኢዮብ ሆይ! እስቲ ዝግ ብለህ አድምጥ፤ እግዚአብሔር የሚያደርጋቸውንም ድንቅ ሥራዎች ልብ ብለህ አስተውል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፥ ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 37:14
14 Referencias Cruzadas  

ሰዎች ሊሠ​ሩት ከሞ​ከ​ሩት በላይ፥ ሥራው ታላቅ እንደ ሆነ አስብ።


ይኸ​ውም፥ ለተ​ግ​ሣጽ ወይም ለም​ድሩ ወይም በም​ሕ​ረት ለሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲ​ሆን ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ውን እን​ዳ​ከ​ና​ወነ ከጨ​ለ​ማም ለይቶ ብር​ሃ​ንን እንደ ፈጠረ እና​ው​ቃ​ለን።


የደ​መ​ና​ትን ክፍ​ሎች፥ አስ​ፈሪ የሆ​ነ​ው​ንም የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን አወ​ዳ​ደቅ ያው​ቃል።


ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤ ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤ እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


ዘሩ በም​ድር ላይ ኀያል ይሆ​ናል፤ የጻ​ድ​ቃን ትው​ል​ዶች ይባ​ረ​ካሉ።


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “አት​ፍሩ፤ ዛሬ የም​ታ​ዩ​አ​ቸ​ውን ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ዩ​አ​ቸ​ው​ምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማዳን እዩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ተመ​ል​ከት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠማማ ያደ​ረ​ገ​ውን ማን ሊያ​ቀ​ናው ይች​ላል?


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።