የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።
ኢዮብ 37:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም፥ ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም በምሕረት ለሚያገኘው እንዲሆን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችን ለመቅጣት ደመና ያመጣል፤ ወይም በዚሁ ምድሩን አጠጥቶ ፍቅሩን ይገልጻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ዝናብን የሚያዘንበው፥ ምድርን ለማረስረስ፥ ሰዎችን ለመቅጣት፥ ወይም ፍቅሩን ለመግለጥ ነው። |
የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።
የሳኦልን አጥንትና የልጁን የዮናታንን አጥንት፥ የተሰቀሉትንም ሰዎች አጥንት በብንያም በአባቱ በቂስ መቃብር አጠገብ ቀበሩአቸው፤ ንጉሡም ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ምድርን ሰማት።
ወዲያ ወዲህም እስኪመላለስ ድረስ ሰማዩ በደመናና በነፋስ ጨለመ፤ ትልቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክዓብም በሰረገላ ተቀምጦ እያለቀሰ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ።
ሦስት ቀንም ሳያልፍ በዘጠነኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን የይሁዳና የብንያም ሰዎች ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሕዝቡም ሁሉ ስለዚህ ነገርና ስለ ታላቁ ዝናብ እየተንቀጠቀጡ በእግዚአብሔር ቤት ፊት ባለው አደባባይ ተቀመጡ።
እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ምግብን በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የበልጉንና የመከሩን ዝናብ ያዘንብላችኋልና።