ኢዮብ 37:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ፥ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ፥ ፈቃዱ ወደ መራችው ይዞራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዘዘውን ለመፈጸም፣ እርሱ በሚሰጠው መመሪያ፣ በመላው የምድር ገጽ ላይ ይሽከረከራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረትም ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናዎች በጌታ መሪነት በምድር ዙሪያ ይዞራሉ፤ የሚያግዛቸውንም ትእዛዞች ይፈጽማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራል። |
እንዳይነሡም፥ ምድርንም እንዳይወርሱ፥ የዓለሙንም ፊት በጦርነት እንዳይሞሉ በአባቶቻቸው በደል ይገድሉአቸው ዘንድ ልጆችህን አዘጋጅ።”
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
እናንተ የጽዮን ልጆች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ ምግብን በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የበልጉንና የመከሩን ዝናብ ያዘንብላችኋልና።
መከር ሳይደርስ ገና ከሦስት ወር በፊት ዝናብን ከለከልኋችሁ፤ በአንድም ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ በአንድ ወገን ዘነበ፤ ያልዘነበበትም ወገን ደረቀ።
እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውሕሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።