ኢዮብ 36:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ የበደለኞችን ሕይወት አያድንም፤ ለችግረኞች ግን ፍርዱን ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ በደለኛን በሕይወት አይጠብቅም፥ ለችግረኞች ግን ይፈርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ክፉ ሰዎች በሕይወት እንዲኖሩ አያደርግም፤ ለተጨቈኑ ሰዎች ግን በቅንነት ይፈርድላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የበደለኞችን ሕይወት አያድንም፥ ለችግረኞች ግን ፍርዱን ይሰጣል። |
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤