ኃጥኣንን ግን አያድናቸውም እግዚአብሔርን ያዩ ዘንድ አይወዱምና፥ ሲገሥፃቸውም አይሰሙምና።
ባይሰሙ ግን፣ በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
ባይሰሙ ግን በሰይፍ ይጠፋሉ፥ ያለ እውቀትም ይሞታሉ።
እርሱን ካልሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ በድንቊርና እንዳሉም ይሞታሉ።
ከጨለማ ተመልሶ እንዲወጣ ተስፋ የለውም፥ ለሰይፍም ኀይል ፈጽሞ ተዳርጎአል።
ነፍሱን ከሞት ያድናታል፤ በሰይፍም እንዳይጠፋ ይጠብቀዋል።
“ግብዞች ግን በልባቸው ቍጣን ያዘጋጃሉ፤ እርሱም ባሰራቸው ጊዜ አይጮኹም።
እፍ ብሎባቸዋልና ይደርቃሉ፥ ጥበብም የላቸውምና ይጠፋሉ።
እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።
እንቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ይደርስበታል።
አንዱ ከሌላው ርቆ አይቆምም፤ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ይሮጣሉ፤ በመሣሪያቸው ላይ ይወድቃሉ፤ እነርሱም አይጠፉም።
ነገር ግን ክፉ ብትሠሩ እናንተም፥ ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።”