ኢዮብ 34:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሣለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣት፥ እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዝን እንደ ውሃ የሚጠጣት፣ እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንደ ኢዮብ በእግዚአብሔር ላይ የሚያፌዝ ሰው ከቶ ይገኛልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሎአልና ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ መሳለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? |
እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔ፥ ለባልንጀራው መሣለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ ጻድቁና ንጹሑ ሰው መሣለቂያ ሆኖአል።
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
“የዚህንም ርግማን ቃሎች በሰማችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስንፍና በማድረግ ሄጃለሁና ይቅር ይለኛል’ የሚል ቢኖር የበደለኛ ፍዳ ካልበደለ ጋር እንዳይተካከል፥