ኢዮብ 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዴን ሐሰተኛ አደረገብኝ፤ በደልም ሳይኖርብኝ በግፍዕ መከራን እቀበላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነተኛ ብሆንም፣ እንደ ውሸታም ተቈጥሬአለሁ፤ በደል ባይኖርብኝም፣ በማይፈወስ ቍስል ተመትቻለሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፥ ምንም ባልበድል ቁስሌ የማይፈወስ ነው ብሏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እውነተኛ ስሆን፥ እንደ ውሸተኛ ተቈጠርኩ፤ ምንም በደል ሳይኖርብኝ በማይፈወስ ቊስል እሠቃያለሁ’ ብሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፥ ምንም ባልበድል ቍስሌ የማይፈወስ ነው ብሎአል። |
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።