ኢዮብ 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ለራሳችን እንምረጥ፤ በመካከላችንም ምን እንደሚሻል እንወቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚበጀንን እንምረጥ፣ መልካሙንም ዐብረን እንወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍትሕን እንምረጥ፥ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትክክለኛ የሆነውን ነገር መርምረን እንወቅ፤ መልካሙንም ነገር አብረን እንማር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፥ መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ። |
ይህን ዓለም አትምሰሉ፤ ልባችሁንም አድሱ፤ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን፥ ፍጹሙንም መርምሩ።
ከዚያም በኋላ ያያት ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲህ ያለ ነገር የሆነበት ጊዜ የለም፤ የታየበትም ጊዜ የለም፤” ያም ሰው እነዚያን የላካቸውን ሰዎች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በሏቸው፦ እስራኤል ከግብፅ ከወጡ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ እንዲህ የሆነበት ጊዜ አለን? እናንተ ተመካከሩበት፤ የሚበጀውንም ተነጋገሩ።”