እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ኢዮብ 33:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተፈጠርህ ነህ፥ የሁላችንም ተፈጥሮ ከዚያው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤ የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔም እንዳንተ ከጭቃ የተቀረጽሁ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ እኔና አንተ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ነን፤ እኔም የተፈጠርኩት ከጭቃ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ። |
እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ፈጠረው፤ በፊቱም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ!
ይልቁንም ከአንድ ዐይነት ጭቃ የተፈጠርን እኛ፥ በተፈጠርንበት የጭቃ ቤት የሚኖሩትን እንደ ብል ይጨፈልቃቸዋል።
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።