ኢዮብ 33:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ነገር ልትመልስልኝ ትችል እንደ ሆነ ታገሠኝ፥ እኔም እነግርሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትችል ከሆነ መልስልኝ፤ ተዘጋጅተህም በፊቴ ቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይቻልህ እንደሆነ መልስልኝ፥ የምትለውን አዘጋጅተህ በፊቴ ቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምትችል ከሆነ ለንግግሬ መልስ ስጠኝ፤ ክርክሮችህን አመቻችተህ ቆመህ ተከራከረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይቻልህ እንደ ሆነ መልስልኝ፥ ቃልህንም አዘጋጅተህ በፊቴ ቁም። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ማልደህ ተነሣ፤ በፈርዖንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወርዳል፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ።