ኢዮብ 31:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርምጃዬ ከመንገዱ ፈቀቅ ብሎ እንደ ሆነ፥ ልቤም ዐይኔን ተከትሎ እንደ ሆነ፥ ጉቦም በእጄ ተጣብቆ እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርምጃዬ ከመንገድ ወጥቶ፥ ልቤም ዓይኔን ተከትሎ፥ ነውርም ነገር ከእጄ ጋር ተጣብቆ እንደሆነ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከትክክለኛው መንገድ ወጥቼ እንደ ሆነ፥ ዐይኔ ያየውን ሁሉ ልቤ ጐምጅቶ እንደ ሆነ፤ እጄም በኃጢአት አድፎ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርምጃዬ ከመንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም ዓይኔን ተከትሎ፥ ነውርም ከእጄ ጋር ተጣብቆ እንደ ሆነ፥ |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው።
“የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ሰዎች በልባቸው ጣዖቶቻቸውን አኑረዋል፤ የበደላቸውንም መቅሠፍት በፊታቸው አቁመዋል፤ እኔስ ለእነርሱ መልስ ልመልስላቸውን?
ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም ዘንድ ከሚቀመጡ መጻተኞች የሚሆን፥ ከእኔ ተለይቶ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም መቅሠፍት በፊቱ የሚያቆም ሰው ሁሉ ስለ እኔ ይጠይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር በራሴ እመልስለታለሁ።
በዚያ በተማረኩበት በአሕዛብ ዘንድ ከእናንተ የዳኑት ያስቡኛል፤ ለሰሰኑበት፥ ከእኔም ለራቁበት ለልቡናቸው፥ ለሰሰኑ፥ ጣዖትንም ለተከተሉ ለዓይኖቻቸው ማልሁ፤ ጣዖቶቻቸውን ሁሉ እንዳመለኩ መጠን ስለ ሥራቸው ክፋት ፊታቸውን ይነጫሉ።
እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ።