ኢዮብ 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ያውቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በጽድቅ ሚዛን ይመዝነኝ፤ ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በትክክለኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ በቅንነት መጽናቴንም ይወቅ። |
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።
“እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤
አትመኩ፤ የኵራት ነገሮችንም አትናገሩ፤ ፅኑዕ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ዙፋኑን ያዘጋጃል።