ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር።
ኢዮብ 31:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ሕዝብ የተነሣ በፊታቸው ለመናገር አፍሬ እንደ ሆነ፥ ድሃውም ከደጄ ባዶውን ወጥቶ እንደ ሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን በመፍራት፣ የወገኖቼንም ንቀት በመሸሽ፣ ወደ ደጅ ሳልወጣ፣ ዝም ብዬ ቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሕዝብ ብዛት የተነሣ ፈርቼ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከደጅ ያልወጣሁ እንደሆነ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቡ ብዛት አስፈርቶኝና፥ የቤተሰብም ነቀፋ አስደንግጦኝ ጸጥ ብዬ በቤት ውስጥ የተደበቅኹበት ጊዜ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሕዝብ ብዛት ፈርቼ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከደጅ ያልወጣሁ እንደ ሆነ፥ |
ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር።
ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮዳሔ ልጆች አንዱ ለሐሮናዊው ለሰንባላጥ አማች ነበረ፤ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።
በልቤም አሰብሁ፤ ታላላቆቹንና ሹሞቹንም፥ “ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ወለድ ትወስዳላችሁ” ብዬ ተጣላኋቸው፤ ትልቅም ጉባኤ ሰበሰብሁባቸው።
እርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፤ ሂዱና በሰፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፤ እያንዳንዱም ወንድሙን፥ እያንዳንዱም ጎረቤቱን፥ እያንዳንዱም የቅርቡን ይግደል” አላቸው።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፥ “ይህችን ነፍስ የፈጠረልን ሕያው እግዚአብሔርን! አልገድልህም፤ ነፍስህንም ለሚሹ ለእነዚህ ሰዎች እጅ አሳልፌ አልሰጥህም” ብሎ በቈይታ ለኤርምያስ ማለ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ኤርምያስን፥ “ወደ ከለዳውያን በኰበለሉ በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል፤ እነርሱም ያፌዙብኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።