ኢዮብ 31:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጻተኛው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመጣው ሁሉ እከፍት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ቤቴ ለመንገደኛው ዘወትር ክፍት ስለ ነበር፣ መጻተኛው በጐዳና ላይ አያድርም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዳው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤቴን ለመንገደኞች ክፍት አደርግ ስለ ነበረ፥ በውጪ የሚያድር እንግዳ ከቶ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጻተኛው ግን በሜዳ አያድርም ነበር፥ ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፥ |
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
በገባዖንም ገብተው ያድሩ ዘንድ ወደዚያ አቀኑ። ገብተውም በከተማው አደባባይ በተቀመጡ ጊዜ ወደ ቤቱ የሚያስገባቸውና የሚያሳድራቸው አልነበረም።
ዐይኑንም አንሥቶ መንገደኛውን በከተማው አደባባይ አየ፤ ሽማግሌውም፥ “ወዴት ትሄዳለህ? ከወዴትስ መጣህ?” አለው።