ኢዮብ 30:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ሕማሜ መሰንቆ፥ ልቅሶዬም በገና ሆነብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገናዬ ለሐዘን፣ እንቢልታዬም ለልቅሶ ተቃኝቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ መሳርያ ሆነ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስታዬን እገልጥባቸው የነበሩት በገና እና እምቢልታ አሁን የሐዘን እንጒርጒሮዬ ማሰሚያ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ ቃል ሆነ። |
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።