ኢዮብ 30:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍርበቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥንቶቼም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆዳዬ ጠቊሮ ተገለፈፈ፤ ሰውነቴም በትኩሳት ተቃጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቁርበቴ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኵሳት የተነሣ ተቃጠለች። |
ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም፤ ቀኑንም ሁሉ መከራ አጸናብኝ።
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል።
እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።