ኢዮብ 30:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ራሴ ልታነቅ በወደድሁ ነበር ይህም ባይሆን ሌላው እንዲሁ እንዲያደርግልኝ እለምናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣ በርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ሰው በወደቀ ጊዜ እጅ አይዘረጋምን? በጥፋቱስ ጊዜ አይጮኽምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ የተቸገረ ሰው ለእርዳታ እጁን ዘርግቶ ሲጮኽ በእርግጥ ማንም ሰው አያጠቃውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሰው በወደቀ ጊዜ እጁን አይዘረጋምን? በጥፋቱስ ጊዜ አይጮኽምን? |
የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ!
አቤቱ ጠላቶችህ ሁሉ እንዲሁ ይጥፉ፤ ወዳጆችህ ግን ፀሐይ በኀይሉ በወጣ ጊዜ እንደሚሆን፤ እንዲሁ ይሁኑ። ምድሪቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረፈች።