ኢዮብ 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋይዋ እንደ ሰንፔር፥ ወርቅዋም እንደ አፈር የሆነ መሬት አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያ ድንጋዮችዋ የሰንፔር መከማቻ ናቸው፥ የወርቅም ድቃቂ ይገኛል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰንፔር የተባለው ዕንቊ በድንጋዮችዋ ውስጥ ይገኛል፤ በዐፈርዋም ውስጥ ወርቅ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይዋ የሰንፔር ስፍራ ነው፥ የወርቅም ድቃቂ አለው። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም የቆመበትን ቦታ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ፥ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።
እጆቹ የተርሴስ ፈርጥ እንዳለባቸው እንደ ለዘቡ የወርቅ ቀለበቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰንፔር ዕንቍ እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥
አንቺ የተቸገርሽ የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፥ እነሆ፥ ድንጋዮችሽን የሚያበሩ አደርጋለሁ፤ መሠረትሽንም የሰንፔር አደርገዋለሁ።
የከተማይቱም ቅጥር መሠረት በከበረ ድንጋይ ሁሉ ተጌጦ ነበር፤ ፊተኛው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥