“እንግዲያ ጥበብ ከወዴት ትገኛለች? የማስተዋልስ ሀገሯ ወዴት ነው?
“ታዲያ፣ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? ማስተዋልስ የት ትገኛለች?
“እንግዲያውስ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
ታዲያ፥ ጥበብ ከየት ትመጣለች? ማስተዋልስ ከወዴት ትገኛለች?
እንግዲያሳ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
“ነገር ግን ጥበብ ወዴት ትገኛለች? የጥበብስ ሀገርዋ ወዴት ነው?
በሰው ሁሉ ዘንድ ተረስታለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሰውራለች።
“እግዚአብሔር መንገድዋን አሳመረ፥ እርሱም ስፍራዋን ያውቃል።
ሰውንም፦ ‘እነሆ፥ እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራቅም ማስተዋል ነው’ ” አለው።
እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤
በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።