ኢዮብ 28:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፈሳሹንም ጥልቀት ይገልጣል። ኀይሉንም በብርሃን ይገልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤ የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዞችን መነሻዎች ይፈልጋል፥ የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወንዞቹን ምንጮች ይገድባል፤ በምድር ውስጥ የተደበቀውንም ሀብት ያገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሳሹም እንዳይንጠባጠብ ይገድባል፥ የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል። |
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።