ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፤ ዐይኔም የከበረውን ነገር ሁሉ ታያለች።
በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።
ከድንጋይ ውስጥ መተላለፍያ ይሠራል፥ ዓይኑም ዕንቁን ሁሉ ታያለች።
አለትን ሰንጥቆ መሿለኪያ መንገድ ያበጃል፤ ውድ የሆኑ የማዕድን ድንጋዮችንም ያገኛል።
ከድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያ ይወቅራል፥ ዓይኑም ዕንቍን ሁሉ ታያለች።
የፈሳሹንም ጥልቀት ይገልጣል። ኀይሉንም በብርሃን ይገልጣል።
ሰው ወደ ቡላድ ድንጋይ እጁን ይዘረጋል፥ ተራራዎችንም ከመሠረታቸው ይገለብጣቸዋል።
በሁሉ ነገር ጠንቃቃ ለሆነ ብዙ ትርፍ አለው። ደስታን ፈላጊና ሰነፍ ግን ችግረኛ ነው።
በዕውቀት ከከበረውና ካማረው ሀብት ሁሉ ጓዳዎች ይሞላሉ።
በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፣ ቀስትህንም ገተርህ፣ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።