ኢዮብ 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ይሰወራል፤ አያበራምም፤ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሓን አይደሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቱ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፣ ከዋክብትም ንጹሓን ካልሆኑ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን ካልሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ እንኳ ደማቅ አይደለችም፤ ከዋክብትም በእርሱ ፊት ንጹሖች አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። |
ጣራቸው ይፈርሳል፤ ግድግዳቸውም ይወድቃል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፥ በሽማግሌዎቹም ፊት ይከብራልና።