ኢዮብ 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተክላቸው በምድር ላይ ሲደርቅ ያያሉ። ያላቸውም ድሀኣደጉን በዘበዙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድርቅና ሙቀት የቀለጠውን በረዶ ከቦታው እንደሚያስወግድ፣ ሲኦልም ኀጢአተኞችን ትነጥቃለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድርቅና ሙቀት የበረዶውን ውኃ ያጠፋሉ፥ እንዲሁ ሲኦል በደለኞችን ታጠፋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረዶ በሙቀት ቀልጦ ውሃውም በድርቅ እንደሚጠፋ፥ ኃጢአተኞችም ሞተው በሙታን ዓለም ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድርቅና ሙቀት የአመዳዩን ውኃ ያጠፋሉ፥ እንዲሁ ሲኦል በደለኞችን ታጠፋለች። |
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።