ኢዮብ 23:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን ልቤን አቀለጠው፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አስጨንቆኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ ሁሉን ቻይ አምላክ አስደነገጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ልቤን አባብቶታልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልቤ እንዲዝል አደረገው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ልቤን አባብቶታልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል። |
“መንፈስ ከእኔ ይወጣልና፥ የሁሉንም ነፍስ ፈጥሬአለሁና ለዘለዓለም አልቀስፋችሁም፤ ሁልጊዜም አልቈጣችሁም።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፤ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፤ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ ይመጣል፤ በምድርም ላይ ግፍ ይነግሣል፤ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ዛሬ ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ትሄዳላችሁ፤ ልባችሁ አይታወክ፤ አትፍሩ፤ አትሸበሩ፤ ከፊታቸውም ፈቀቅ አትበሉ፤