ኢዮብ 20:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ዘንድ የኀጢአተኛ ሰው እድል ፋንታው፥ ከሚያየው ከፈጣሪውም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች የወሰነው ዕድል ፈንታ፣ ከአምላክም ዘንድ የተመደበላቸው ቋሚ ቅርስ ይህ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከአምላክ የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለዐመፀኞች የወሰነላቸው ዕድል ፈንታ፥ የክፉ ሰዎች ዋጋ ይኸው ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው። |
ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የኀጢአተኛ እድል ፋንታ ናት፥ ግፈኞችም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበሏት ሀብት ናት።