ኢዮአብም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው።
ኢዮብ 20:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀስቱም በሥጋው ውስጥ ያልፋል። ክፉም ነገር በሰውነቱ ይመላለሳል፤ ፍርሀትም ይወድቅበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስቱን ከጀርባው፣ የሚያብለጨልጨውንም ጫፍ ከጕበቱ ይመዝዛል፤ ፍርሀትም ይይዘዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻውም ዘልቆ በስተጀርባው ይወጣል፤ የሚያብለጨልጨው ጫፉ ጒበቱን በጣጥሶ ያልፋል፤ በታላቅ ፍርሀትም ልቡ ይሸበራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥ ፍርሃትም ይወድቅበታል። |
ኢዮአብም፥ “እኔ ከአንተ ጋር እንዲህ እዘገይ ዘንድ አልችልም” ብሎ ሦስት ጦሮች በእጁ ወሰደ፤ አቤሴሎምም ገና በዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሕያው ሳለ በልቡ ላይ ተከላቸው።
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።
ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።